Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና ተመድ ተፈናቃዮችን በመደገፍ ረገድ ትብብራቸውን ለማጠናከር ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችን በመደገፍ ረገድ ትብብራቸውን ለማጠናከር ተስማሙ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ የተመድ ዋና ፀሀፊ የሀገር ውስጥ መፈናቀል መፍትሄዎች ልዩ አማካሪ ከሆኑት ሮበርት ፓይፐርን ጋር ዛሬ በአዲስ አበባ ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችን ወደቀዬአቸው ለመመለስ የኢትዮጵያ መንግስት እየወሰዳቸው የሚገኙ ልዩ ልዩ እርምጃዎችን አምባሳደር ምስጋኑ አብራርተዋል።

ሮበርት ፓይፐር በበኩላቸው የኢትዮጵያ መንግስት ለሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ከለላ ለመስጠት እና ለመርዳት የሚያስችለውን አዋጅ ለማጠናቀቅ የሚያደርገውን እርምጃ አድንቀዋል።

መንግስት በርካታ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችን ወደ መጡበት አካባቢ መመለስ መቻሉን አድንቀው ይህም የጸጥታ ሁኔታ መሻሻል እና ሌሎች ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ያሳያል ብለዋል።

እንዲሁም በውይይታቸው ላይ በሰብዓዊ ድጋፍ ሰጭዎች እና የሰላም ተዋናዮች መካከል ትብብር እና ቅንጅት እንደሚያስፈልግ መነሳቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.