Fana: At a Speed of Life!

ከ13 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ ጥራታቸውን ያልጠበቁ የምግብ ምርቶች እና የሕክምና መሣሪያዎች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ታገዱ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከ13 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ ጥራታቸውን ያልጠበቁ የምግብ ምርቶች እና የሕክምና መሣሪያዎች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ መታገዳቸውን የኢትዮጵያ የምግብ እና መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን አስታወቀ።

ጥራታቸውን ያልጠበቁ የምግብ ምርቶች እና የሕክምና መሣሪያዎች ወደ ሀገር እንዳይገቡ የታገዱት በ2013 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት መሆኑ ተጠቁሟል።

ከዚህ ባለፈም 14 የምግብ ምርቶች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ማገዱን ባለሥልጣኑ ገልጿል።

በሩብ ዓመቱ እንዳይገቡ ከታገዱት የሕክምና መሣሪያዎች ውስጥ የእጅ ጓንት፣ የአፍ እና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብሎች እና የሙቀት መሣሪያዎች ይገኙበታል ተብሏል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.