Fana: At a Speed of Life!

ከ228 ሚሊየን በላይ ችግኞችን ለመትከል ዝግጅት እያደረኩ ነው – የደቡብ ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በዘንድሮው የአረንጎዴ  አሻራ መርሀግብር ከ228 ሚሊየን በላይ ችግኞችን ለመትከል ዝግጅት እያደረገ መሆኑን የደቡብ ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ ገለጸ።

የመምሪያው ሀላፊ አቶ ቃልኪዳን ሸፈራው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት  እንደተናገሩት በዞኑ የአረንጎዴ አሻራ መርሀግብሩን የተሳካ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ ነው ።

ችግኞቹን ለመትከል ከ43 ሺህ በላይ ሄክታር መሬት መለየቱን የተናገሩት ሀላፊው የችግኝ ጉድጎድ ቁፋሮው እስከ ግንቦት 30 ይጠናቀቃል ብለዋል።

የካርታ ልየታና የጂፒኤስ ንባብ ስራው በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን እና በዞን ደረጃ በአንድ ቀን ከ47 ሚሊየን በላይ ችግኞችን ለመትከል ታቅዷል  ያሉት ሀላፊው ይህን ለመተግበር የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ገልፀዋል።

በከድር መሀመድ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.