Fana: At a Speed of Life!

ወደ ሰው የሚተላለፍ የዝንጀሮ ፈንጣጣ በአውሮፓ ሀገራት እየተሥፋፋ ነው ተባለ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ወደ ሰው የሚተላለፍ የዝንጀሮ ፈንጣጣ በአውሮፓ ሀገራት እየተሥፋፋ መሆኑን የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ፡፡
 
ድርጅቱ እስካሁን ድረስ በአውሮፓ ሀገራት 80 የሚደርሱ የወረርሽኙ ተጠቂ ሰዎች መመዝገባቸውን አመላክቷል፡፡
 
ፖርቹጋልና ስፔን ከ40 በላይ ዜጎቻቸው በቫይረሱ ሳይጠቁ እንዳልቀረ የሀገራቱ የጤና ቁጥጥር ባለሥልጣናት ይፋ አድርገዋል፡፡
 
በስፔን በቫይረሱ የተጠቁት 23 በወጣትነት ዕድሜ ላይ የሚገኙ ወንዶች ናቸው ተብሏል፡፡
 
ቫይረሱ በዋናነት በግብረ-ስጋ ግንኙነት ሳይተላለፍባቸው እንዳልቀረም የስፔን የጤና ባለሥልጣናት ጠቁመዋል፡፡
 
ጀርመን ፣ ፈረንሳይ፣ እንግሊዝ እና አሜሪካም ቫይረሱ በሀገራቸው እንደተከሰተ ማስታወቃቸውን ሲጂቲ ኤን ዘግቧል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.