Fana: At a Speed of Life!

ዓለም ላይ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ95 ሚሊየን አልፏል

አዲስ አበባ ፣ ጥር 10 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም ላይ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 95 ሚሊየን 488 ሺህ 91 መድረሱ ተገለጸ።

በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 2 ሚሊየን 39 ሺህ 706 መድረሱም ነው የተገለጸው።

በአንጻሩ 68 ሚሊየን 196 ሺህ 88 ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ ማገገማቸው ነው የተነገረው።

ከዚህ ውስጥ በአሜሪካ 24 ሚሊየን 482 ሺህ 50 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲያዙ፥ 407 ሺህ 202 ሰዎች ደግሞ ለህልፈት ተዳርገዋል።

ይህም ዓለም ላይ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን የቫይረሱ ተጠቂዎች በማስመዝገብ ቀዳሚዋ አድርጓታል።

በሕንድ ደግሞ ከ10 ሚሊየን በላይ ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል።

ብራዚል፣ ሩሲያ፣ ብሪታንያ እና ፈረንሳይ ደግሞ ተከታዮቹን ደረጃዎች ይዘዋል።

ምንጭ፦ ዎርልድ ኦ ሜትር

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.