Fana: At a Speed of Life!

የሀረሪ ክልል የካቢኔ አባላት የአንድ ወር ደሞዛቸውን ለመከላከያ ሰራዊት ለገሱ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀረሪ ክልል የካቢኔ አባላት ለሁለተኛ ጊዜ የአንድ ወር ሙሉ ደሞዛቸውን ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ለገሱ፡፡
የክልሉ የካቢኔ አባላት ዛሬ ባካሄዱት ስብሰባ ነው የአንድ ወር ደሞዛቸውን ለመስጠት የወሰኑት።
የካቢኔ አባላቱ ከወራት በፊትም የወር ደሞዛቸውን መለገሳቸው የሚታወስ ነው።
የመስተዳድር ምክር ቤት አባላቱ በቀጣይም ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ነው የገለፁት።
በተሾመ ኃይሉ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.