Fana: At a Speed of Life!

የሃገራት መሪዎች በአይሁዳውያን ላይ የተፈጸመውን የዘር ጭፍጨፋ 75ኛ አመት እየዘከሩ ነው

አዲስ አበባ፣ጥር 14፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የተለያዩ ሃገራት መሪዎች የሃገራት መሪዎች በአይሁዳውያን ላይ የተፈጸመውን የዘር ጭፍጨፋ 75ኛ አመት እየዘከሩ ነው።

በመታሰቢያ ስነ ስርዓቱ ላይ የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን፣ የእስራኤሉ አቻቸው ኢማኑኤል ማክሮን፣ የጀርመኑ ፕሬዚዳንት ፍራንክ ዋልተር ስቴይንሜዬር እና የአሜሪካው ምክትል ፕሬዚዳንት ማይክ ፔንስ ተገኝተዋል።

መሪዎቹ በናዚ አገዛዝ ፖላንድ በሚገኘው ኦሽዊትዝ ካምፕ ለተጨፈጨፉ አይሁዶች መታሰቢያ በሆነው በያድ ቫሽም ነው የተሰባሰቡት።

በቆይታቸውም በወቅቱ ሰለባ ለሆኑ እስራኤለውያን የአበባ ጉንጉን ያስቀምጣሉ።

በፕሮግራሙ ላይ የፖላንዱ ፕሬዚዳንት ንግግር አያደርጉም መባሉን ተከትሎ አለመገኘታቸው ታውቋል።

በወቅቱ በአዶልፍ ሂትለር በሚመራው የናዚ አገዛዝ በአብዛኛው እስራኤለውያን የሆኑ ከ1 ሚሊየን በላይ ሰዎች ተገድለዋል።

መድረኩ ዓለም አቀፍ የመሪዎች ጥምረት ለመገንባት፣ ትብብርን ለማጎልበት እና መሰል የዘረኝነት ክስተት እንዳይከሰት የሚያወግዝ ጠንካራ መልዕክት ለማስተላለፍ ወሳኝ መሆኑ ተገልጿል።

በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ለአይሁዳውያን የሰቆቃ ስፍራ የነበረው ኦሽዊትዝ ማጎሪያ ካምፕ በፈረንጆቹ 1945 በሩሲያ ወታደሮች አማካኝነት መዘጋቱ ይታወሳል።

ምንጭ፦ ቢ.ቢ.ሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.