Fana: At a Speed of Life!

የህዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ የፊታችን ሰኞ ይካሄዳል  

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)  የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የፌዴሬሽን እና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤቶች 5ኛ የፓርላማ ዘመን 6ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ 1ኛ መደበኛ የጋራ ስብሰባ መስከረም 25 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚያካሂዱ ተገለፀ፡፡

የፌዴሬሽን ምክር ቤት መደበኛ ሰብሰባውን አስመልክቶ ለአባላቱ ባስተላለፈው የጥሪ ማስታወቂያ ምክር ቤቱ መደበኛ ስብሰባውን መስከረም 26 እና 27 ቀጥሎ የሚያካሂድ ይሆናል።

የሁለቱ ምክር ቤቶችን የጋራ ስብሰባም የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በሚያደርጉት ንግግር የሚከፈት ይሆናል።

በፕሬዚዳንቷ የመክፈቻ ንግግርም በ2013 በጀት ዓመት የፌደራል መንግስት ትኩረት ሰጥቶ የሚያከናውናቸው ተግባራት ይፋ ይደረጋሉ ተብሎ ነው የሚጠበቀው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.