Fana: At a Speed of Life!

የሶማሊያ መንግስት የፓርላማ አባላት ምርጫ እንዲቀጥል ወሰነ

አዲስ አበባ፣ ጥር 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሊያ መንግስት የተጓተተውን የሀገሪቱን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ምርጫ እንዲቀጥል በመወሰን የምርጫ መርሀ ግብሩን ይፋ አደረገ፡፡

የምርጫ ድምጽ የመስጠት ሂደት ከተጀመረ በኋላ ተቋርጦ የነበረበት የ ጋልሙዱግ ክልል÷ በቀጣዮቹ ቀናት ተጨማሪ 21 የፓርላማ አባላትን እንደሚመርጥም ተወስኗል፡፡

በጠቅላይ ሚኒስትር ሁሴን ሮብሌ ሰብሳቢነት ሚመራው የሀገሪቷ የምክክር ምክር ቤት በጥር ወር መጀመሪያ ባካሄደው ስብሰባ ÷ ሁሉም አስመራጭ ኮሚቴዎች የህዝብ ምክር ቤት አባላት ምርጫውን እንዲያፋጥኑ አሳስቧል።

እያንዳንዱ ፌዴራላዊ ክልልም ምርጫ የሚያካሂድበትን ቀነ ገደብ ከወዲሁ እንዲያሳውቅ ምክር ቤቱ ትዕዛዝ አስተላልፏል፡፡

የሀገሪቱ የፓርላማ ምርጫ የካቲት 25 እንዲካሄድም ስምምነት ላይ መደረሱን ነው ዘ ኢስት አፍሪካን የዘገበው፡፡

በሶማሊያ 275 መቀመጫ ያለውን የታችኛውን ምክር ቤት (የህዝብ ተወካዮች) ለመምረጥ 30 ሺህ የሚሆኑ የጎሳ ተወካዮች የተመደቡ ሲሆን፥ 54 አባላት የሚያካትተውን የላይኛውን ምክር ቤት(ሰኔት) የሚመርጡት ደግሞ የአምስት ክልሎች ህግ አውጪዎች እንደሚሆኑ በአገሪቱ ህግ ተደንግጓል።
የአገሪቱን ፕሬዚደንት የሚመረጠውም የምርጫው ውጤት በይፋ ከተገለጸ በኋላ ሁለቱ ምክር ቤቶች በሚያካሂዱት በጋራ ስብስባ እንደሆነ በህግ ተወስኗል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.