Fana: At a Speed of Life!

የሶማሌ ክልል ካቢኔ በድርቅ ለተጎዱ ዜጎች የሚውል 70 ሚሊየን ብር ተጨማሪ በጀት ላይ ውሳኔ አሳለፈ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ስራ አስፈፃሚ ምክር ቤ (ካቢኔ) ዛሬ ባካሄደው ስብሰባ በድርቅ ለተጎዱ ዜጎች የሚውል 70 ሚሊየን ብር ተጨማሪ በጀትን ጨምሮ በሁለት አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ።
የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዲቃድር ረሺድ ዱዓሌ እንደገለጹት፥ ዛሬ የተካሄደው የክልሉ ስራ አስፈፃሚ ም/ቤት ስብሰባ በሁለት ዋና ዋና አጀንዳዎች ላይ ያተኮረ ነው።
የስራ አስፈፃሚ ምክር ቤቱ በመጀመረያ የተወያየው በክልሉ በተከሰተው የድርቅ አደጋ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ሲሆን÷ በድርቁ የተጠቁ ሰዎችና እንስሳት እስኪያገገሙ ድረስ እርዳታው እንዲቀጥል ምክር ቤቱ መውሰኑንም ኃላፊው ተናግረዋል።
ከዚህ በተጨማሪም በተቀደሰው የረመዳን ወር ህዝበ ሙስሊሙ በሰላም እንዲፆም ህዝብ የሚበዛባቸው እንደ ከተማ አስተዳደሮች፣ የዞን ዋና ከተሞችና የመሳሰሉት አካባቢዎች ለተቸገሩ ወገኖች ድጋፍ የሚውል 70 ሚሊየን ብር ተጨማሪ በጀት ለመበጀት በሥራ አሰፈጻሚ ም/ቤቱ ስብሰባ ላይ ከስምምነት መድረሱንም አቶ አብዲቃድር ረሺድ አብራርተዋል።
ኃላፊው አያይዘውም፥ በጉባኤው የዋጋ ንረት በሚረጋጋበትና ህዝቡን በተለይ በፆም ወቅት መታደግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ማሳለፉን ነው የገለጹት።
የክልሉ መንግስት የዋጋ ንረትን ለመግታት በተመጣጣኝ ዋጋ እህል እንደሚገዛና ለህብረተሰቡ ተደራሽ እንደሚያደርግ መናራቸውን ከሶማሌ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በዚህም የክልሉ ነጋዴዎችና የንግድ ተቋማት ለችግር ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን በማሰብ፥ የህዝቡን ህይወት አደጋ ላይ ሊጥል ከሚችል ከማንኛውም ነገር ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስበዋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.