Fana: At a Speed of Life!

የቻይና የሀኪሞች ቡድን ዚምባብዌ ገባ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 18 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) 10 የልኡካን አባላትን የያዘው የቻይና የሀኪሞች ቡድን ዚምባብዌ ደርሷል።

ቡድኑ  ዚምባብዌ የገባው ሀገሪቱ የኮኖና ቫይረስን ለመከላከል የምታደርገውን ጥረት ለመደገፍ ነው ተብሏል፡፡

ከዚህ ባለፈም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የጤና ትብብር ለማጎልበት ያለመ መሆኑ ተነግሯል።

ቡድኑ ለሚቀጥሉት 12 ወራቶች በፓሪሬናታዋ ሆስፒታል ውስጥ ይቆያልም ነው የተባለው፡፡

የሀኪሞች ቡድን ሃላፊ ዶክተር ሊዎ ዌይ ኪያንግ÷ ሀኪሞቹ ዚምባቡዌ በሚኖራቸው ቆይታ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ከሚያደርጉት ድጋፍ በተጨማሪ የቻይና ባህላዊ መድሀኒቶችን የማስተዋወቅ ስራም ይሰራሉ ብለዋል።

ምንጭ፡-ቢቢሲ

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.