Fana: At a Speed of Life!

የአገው ፈረሰኞች ማህበር ክብረ በዓል እና የፈረስ ፌስቲቫል ለ82ኛ ጊዜ በደመቀ መልኩ ይከበራል

አዲስ አበባ፣ ጥር 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ታሪካዊ ፣ ባህላዊ እና ሀይማኖታዊ ዳራ ያለው በየዓመቱ ጥር 23 የሚከበረው የአገው ፈረሰኞች ማህበር ክብረ በዓል እና የፈረስ ፌስቲቫል ዘንድሮ ለ82ኛ ጊዜ በደመቀ ሁኔታ ይከበራል።
 
የአገው ፈረሰኞች የነፃነት ተጋድሎ ያስመሰከሩና በዓድዋ ጦርነትም ጀግንነታቸውን ያሳዩ መሆናቸው እና ማህበሩ የተመሰረተውም ለዚሁ መታሰቢያነት መሆኑ ተገልጿል።
 
ፈረስ ለአዊ የእርሻ፣ የመጓጓዣ፣ የታመመን ሆስፒታል ማድረሻ፣ ከአጠቃላይ የማህበረሰቡ እንቅስቃሴ ጋር የተቆራኘ መሆኑም ተመልክቷል።
 
በአዊ ባሉ 9 ወረዳዎች 59 ሺህ 300 የአገው ፈረሰኞች አባል ያሉ ሲሆን÷ የተጣላ የሚያስታርቅ ፣ በከተማው ያሉ ህገወጥ ተግባራትን በመቅረፍ ከመንግስት ጋር የሚሰራም ማህበር መሆኑም ተጠቅሷል።
 
82ኛ አመቱን ሊያከብር ዝግጅቱን ያጠናቀቀው ማህበሩ እንደ ሀገር በተካሄደው የህልውና ዘመቻ ከ1 ሺህ 300 በላይ ጦረኛችን ጨምሮ የ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር እና የእንስሳት ድጋፍ አድርጓልም ነው የተባለው።
 
ይህ በየዓመቱ የአገው ፈረሰኞች ማህበር ትልቅ የቱሪስት መስህብ ሆኖ በዩኔስኮ እንዲመዘገብ ጥረት እየተደረገ መሆኑም ተመላክቷል።
 
የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ለማህበሩ በርካታ ስራ ሲሰራ መቆየቱ የተገለጸ ሲሆን÷ ጥር 22 የቱሪስት መዳረሻነቱን ለማስፋት ፣ የፈረስ ፌስቲቫሉ የራሱ የሆነ ማቅረቢያ ቦታን እና ተጠቃሚነትን የተመለከተ የፓናል ውይይይት ያደርጋልም ተብሏል።
 
በውይይቱ የከተማ አስተዳደሩ፣ የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ እና የማህበሩ አባላት፣ ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ ዳያስፖራዎች እና የከተማዋ ነዋሪዎች እንደሚሳተፉም ተገልጿል፡፡
 
በቅድስት ወልዴ
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.