Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ ህብረት በቻድ እና በሶማሊያ ቀውሶች ዙሪያ ሊመክር ነው

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 14 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአፍሪካ ህብረት የሰላም እና ደህንነት ምክር ቤት በቻድ እና በሶማሊያ ቀውሶች  ዙሪያ ሊመክር ነው ፡፡

ምክር ቤቱ ስብሰባውን የሚያካሂደው በቻድ የተቃዋሚ ፓርቲ  ፖለቲከኞች፥ ፕሬዚዳንት ኢድሪስ ዴቢ ከሞቱ በኋላ  የሃገሪቱ ጦር ለፕሬዚዳንቱ ልጅ የአባቱን ቦታ እንዲተካ የሰጡትን ሹመት ከተቃወሙ በኋላ ነው፡፡

ለሶስት አስርት ዓመታት በስልጣን ላይ የቆዩት  የቻዱ ፕሬዚዳንት ከአማፅያን  በተተኮሰባቸው ጥይት ተመተው ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል፡፡

በተመሣይም ሶማሊያም ፕሬዚዳንታዊ እና አካባቢያዊ ምርጫዎችን ተከትሎ  ቀውስ ተጋርጦባታል፡፡

ባለፈው ሳምንት የሃገሪቱ ፓርላማ የፕሬዚዳንት ሞሃመድ አብዱላሂ ፋርማጆን የስልጣን ዘመን አወዛጋቢ በሆነ ሁኔታ ለሁለት ዓመት ማራዘሙ ይታወሳል ።

ምንጭ፡-ቢቢሲ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፦https://www.facebook.com/fanabroadcasting

 

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.