Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ ልማት ባንክ የምግብ እጥረትን ለመከላከል የሚውል የ1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር አጸደቀ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ልማት ባንክ የምግብ እጥረትን ለመከላከል የሚውል 1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር አጽድቋል፡፡

የአፍሪካ ልማት ባንክ በአህጉሩ በሚገኙ ሀገራት የምግብ እጥረትን ለመከላከል የሚውል ነው ያለውን 1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር አጽድቋል።

ባንኩ ያጸደቀው ድጋፍ በዩክሬን ሩስያ ጦርነት የተከሰተውን የአቅርቦት እጥርት ለመሸፈን የሚውል ሲሆን 30 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን እህል ግብይት እንደሚፈጸምብት ተገልጿል።

ድጋፉ ከሩስያና ዩክሬን ወደ አፍሪካ የሚገቡትን ስንዴ፣ ቦቆሎና አኩሪ አተር ምርቶች አቅርቦትን የሚተካ መሆኑ ተመልክቷል።

በተጨማሪም አሁን የጸደቀው ድጋፍ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በራስ አቅም ለመሸፈን የሚያስችልና በመጪው የመሕር ወቅት ለአርሶ አደሮች ምርጥ ዘር ለማቅረብ የሚያስችል መሆኑን ባንኩ ማስታወቁን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.