Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ ቁጥር አንዷ ቢሊየነር በገንዘብ ምዝበራ ውንጀላ ቀረበባቸው

አዲስ አበባ፣ ጥር 14 ፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) አንጎላዊቷ ቁጥር አንድ ቢሊየነር ኢዛቤላ ዶስ ሳንቶስ በገንዘብ ምዝበራ ውንጀላ ቀርቦባቸዋል።

ኢዛቤላ ዶስ ሳንቶስ የሃገሪቱ ጋዝ እና ነዳጅ አውጭ ኩባንያ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆነው በሚሰሩበት ወቅት ወንጀሉን መፈጸማቸውን ጠቅላይ አቃቤ ህግ ሄልደር ፒታ ግሮስ ተናግረዋል።

ይህን ተከትሎም የገንዘብ ምዝበራ፣ ህገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር እና ገንዘብን ወደ ውጭ ሃገር የማሸሽ ወንጀል ፈጽመዋል በሚል ውንጀላ ቀርቦባቸዋል።

ጠቅላይ አቃቤ ህጉ ግለሰቧ ወደ ሃገራቸው ተመልሰው የሚቀርብባቸውን ክስ እንዲከታተሉም ጥሪ አቅርበዋል።

ባለሃብቷ ግን ለደህንነታቸው እንደሚሰጉ በመግለጽ ወደ አንጎላ አልመለስም ብለዋል፡፡

እንዲሁም በቅርቡ እርሳቸውን በተመለከተ በተለቀቁት ሰነዶች የተገለጸውን የሙስና ወንጀል አልፈፀምኩም ሲሉ ተደምጠዋል።

ኑሯቸውን በእንግሊዝ ያደረጉት ቢሊየነሯ በሃገራቸው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የመወዳደር እቅድ እንዳላቸው ገልጸዋል።

ወላጅ አባታቸው ጆዜ ኤድዋርዶ ዶስ ሳንቶስ በፈረንጆቹ 2017 ከስልጣን ከመውረዳቸው አስቀድሞ አንጎላን ለ38 አመታት በፕሬዚዳንትነት መርተዋታል።

ምንጭ፡-ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.