Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ሞተር አልባ ትራንስፖርት ስትራቴጂ ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 26፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሞተር አልባ ትራንስፖርት ስትራቴጂን የትራስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ ይፋ አድርገዋል።

ስትራቴጂው የትራንስፖርት እንቅስቃሴን ለማሻሻልና ሁሉን አቀፍ ልማትን ለማረጋገጥ ሀገሪቱ በሚቀጥሉት አስር ዓመታት ውስጥ የምትተገብራቸውን እርምጃዎች በዝርዝር ያስቀመጠ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የሞተር አልባ ትራንስፖርት አገልግሎት ህብረተሰቡ በቀላሉ ከቦታ ቦታ እንዲንቀሳቀስ የሚያስችል፣ ለሁሉም ተደራሽ የሆነ፣ ወደ ብዙሀን ትራንስፖርት በቀላሉ ተደራሽ እንዲሆኑ የሚያደርግ እና የማህበረሰቡ ጤናም እንዲጠበቅ የበኩሉን የሚያበረክት የትራንሰፖርት ዘርፍ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ ስትራቴጂው ስኬታማ እንዲሆን አስተዋፆ ላበረከቱት ተቋማት መምስጋና ማቅረባቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.