Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ “ለ1 ሚሊየን ወደ አገር ቤት” ዘመቻ ተሳታፊዎች የ30 በመቶ የዋጋ ቅናሽ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 27 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ “ለ1 ሚሊየን ወደ አገር ቤት” ዘመቻ ለሚሳተፉ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የ30 በመቶ የዋጋ ቅናሽ አደረገ።
በቅናሹ ተጠቃሚ የሚሆኑት ከዛሬ ጀምሮ እስከ ፈረንጆቹ ታህሳስ 20 ቀን 2021 ድረስ ትኬት የሚቆርጡና፥ ከፈረንጆቹ ጥር 1 እስከ 31 ቀን 2022 ድረስ ወደ ኢትዮጵያ የሚጓዙ የዘመቻው ተሳታፊ መንገደኞች መሆናቸውን አየር መንገዱ በትዊተር ገጹ አስታውቋል።
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች “የ1 ሚሊየን ወደ አገር ቤት” ዘመቻ ተሳታፊ እንዲሆኑ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት ጥሪ የፈረንጆቹን አዲስ ዓመት በኢትዮጵያ ለማክበር ይፋ የሆነውን 1 ሚሊየን ዳያስፖራ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ወደ አገር ቤት እንዲገቡ የማድረግ ጥሪን እንዲቀበሉ ጠይቀዋል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.