Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ ክልል መንግስት በአርቲስት ኑሆ ጎበና ህልፈት የተሰማውን ሀዘን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥር 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በአርቲስት ኑሆ ጎበና ህልፈተ ህይወት የተሰማውን ሀዘን ገለጸ፡፡
 
የክልሉ መንግስት ባወጣው መግለጫ ÷ አርቲስት ኑሆ ጎበና በአፋን ኦሮሞ ኪነ ጥበብ ዘርፍ እድገት ጉልህ አስተዋጽኦ ማበርከቱን አንስቷል፡፡
 
አርቲስቱ በአፋን አሮሞ እና በሌሎች ቋንቋዎች በርካታ ጥዑም ዜማዎችን ለአድማጭ ማበርከቱም በመግለጫው ተጠቅሷል፡፡
 
ኑሆ ጎበና በጥበብ ስራዎቹ የኦሮሞ ህዝብን ጥያቄዎች ነቅሶ በማውጣት ለህዝብ የኖረ አንጋፋ አርቲስት መሆኑንም አውስቷል፡፡
 
አርቲስቱ በወጣትነት ዘመኑ የደርግ እና የጨቋኙ ህወሓት ቡድን ስርዓት ህዝብ ላይ ሲያደርስ የነበረውን በደል በመቃወም ሲታገል መኖሩም በመገለጫው ተነስቷል፡፡
 
ክልሉ በአርቲስቱ ህልፈት የተሰማውን ሀዘን ገልጾ÷ ለወዳጅ ዘመዶቹ እና ለአድናቂዎቹም መጽናናትን ተመኝቷል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.