Fana: At a Speed of Life!

የኮሮና ቫይረስ በቡርኪና ፋሶ ተገኘ

አዲስ አበባ፣መጋቢት 1፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)በቡርኪና ፋሶ  ሁለት የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች መገኘታቸውን የሃገሪቱ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታውቋል።

የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ክላውዲን ሉጉዌ ÷የቫይረሱ ተጠቂዎች ባልና ሚስት ሲሆኑ በቅርቡ ከፈረንሳይ የተመለሱ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

ባለትዳሮቹ ሰኞ በተደረገላቸው ምርመራ የቫይረሱ  ተጠቂ መሆናቸው የተረጋገጠ ሲሆን÷ በአሁኑ ወቅትም በለይቶ ማቆያ ስፍራ ክትትል እየተደረገላቸው  ነው ብለዋል፡፡

ከባለትዳሮቹ ጋር የቅርብ ግንኙነት ያለው   ሦስተኛ ሰውም  ክትትል እየተደረገለት እንደሚገኝም ተጠቁሟል።

ይህን ተከትሎም ቡርኪና ፋሶ የኮሮና ቫይረስ  የተገኘባት 10ኛዋ የአፍሪካ ሀገር ሆናለች።

በአሁኑ ሰዓት በአፍሪካ   በኮሮና ቫይረስ የተጠቁ 100 ሰዎች እንደሚገኙ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

ምንጭ፡-ቢ.ቢሲ

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.