Fana: At a Speed of Life!

የወባ በሽታን 70 በመቶ መቀነስ ይቻላል – ጥናት

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካውያን ወጣቶች እና ሕፃናት ላይ የተሠራ አንድ ጥናት እንዳመላከተው:- በወባ በሽታ ምክንያት የሚደርስ ሕመም እና የሞት አደጋን 70 በመቶ መቀነስ ይቻላል፡፡

የእንግሊዝ ሜዲካል ጆርናል ላይ የታተመው ይህ ጥናት:- በብሩኪናፋሶ የሚገኙ እድሜያቸው ከ 17 ወራት በታች የሆኑ 6 ሺህ ሕፃናት ላይ ነው የተካሄደው፡፡

የለንደን አጥኚዎችን ዋቢ ያደረገው የእንግሊዝ ሜዲካል ጆርናል:- በሽታውን የመከላከል እና የማከም ስራ ከመስራት በተጨማሪ ክትባት መስጠት አስገራሚ ውጤት ይኖረዋል ብሏል፡፡

ከሦስት ዓመታት በላይ በተደረገ ሙከራ ከአስከፊው የወባ ትንኞች መራቢያ ወቅት በፊት ሶስት ክትባቶችን እና ሌሎች መድኃኒቶች መገኘታቸውም ነው መረጃው ያመላከተው፡፡

እንደ ሳይንቲስቶቹ:- ክትባቱንና መድሐኒቶቹን በጥምረት በመጠቀም የተገኘው የፈጠራ ውጤት አስደናቂ ነው።

ክትባቱ ብሩኪናፋሶን ተከትሎ በጋና ፣ በኬንያ እና በማላዊ ላሉ ከ740ሺህ በላይ ሕፃናት ተደራሽ ሆኗል፤ በመደበኛ የልጆች ክትባት መርሃ ግብርነት ተካቷልም ነው የተባለው፡፡

በማሊ የሚገኙ ተመራማሪዎችም:- ይህን አዲስ የፈጠራ ውጤት በሀገሪቷ ተግባራዊ ለማድረግ “ፈጣን የፖሊሲ ውሳኔ” በጉጉት እንደሚጠብቁ ተናግረዋል።

በሙከራ ሂደቱ በልጆች ላይ የጎንዮሽ ጉዳት አለማስከተሉ ነው የተጠቀሰው።

በወባ በሽታ ምክንያት ሕይወታቸውን ከሚያጡ ሰዎች 400 ሺህ ያህሉ እድሜያቸው ከአምስት በታች እንደሆነ ቢቢሲ አስታውሶ:- አሁንም የወባ በሽታ ከሠሃራ በታች ላሉ ሀገራት ስጋት ሆኖ መቀጠሉን አመላክቷል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.