Fana: At a Speed of Life!

የዓለም ሀገራትና ተቋማት መሪዎች በዓለም ዙሪያ 1 ትሪሊየን ችግኝ ለመትከል ቃል ገቡ

አዲስ አበባ፣ ጥር 14፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የዓለም ሀገራት መሪዎች እና የዓለም አቀፍ ተቋማት መሪዎች በዓለም ዙሪያ 1 ትሪሊየን ችግኝ ለመትከል ቃል መግባታቸው ተነግሯል።

በስዊዘርላንድ ዳቮስ እየተካሄደ በሚገኘው የዓለም ኢኮኖሚክ ፎረም ላይ በመሳተፍ ላይ የሚገኙ የዓለም ሀገራት መሪዎች እና የዓለም አቀፍ ተቋማት መሪዎች ናቸው 1 ትሪሊየን ችግኝ የመትከል እቅዱን ይፋ ያደረጉት።

ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተያያዘ በሚወስዷቸው እርምጃዎች በብዛት ትችት የሚቀርብባቸው የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕም የ1 ትሪሊየን ችግኝ የመትከል ዘመቻውን መደገፋቸው ነው የተገለፀው።

ባሳለፍነው ማክሰኞ በተጀመረው እና ዛሬ ሶስተኛ ቀኑን በያዘው በስዊዘርላንድ ዳቮስ እየተካሄደ በሚገኘው የዓለም ኢኮኖሚክ ፎረም ላይ የአየር ንብረት ለውጥ ዋነኛው የመወያያ አጀንዳ መሆኑ ነው የተገለፀው።

በዳቮስ እየተካሄደ በሚገኘው የዓለም ኢኮኖሚክ ፎረም ላይም በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የተመራ ከፍተኛ የመንግስት ልኡክ በመሳተፍ ላይ ይገኛል።

ምንጭ፦ aljazeera.com

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.