Fana: At a Speed of Life!

የዓለም የምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ ችግር ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች የሰብአዊ ድጋፍ ለማጠናከር በትጋት እየሰራ መሆኑን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ሰኔ 16፣2014 (ኤፍ ቢሲ) የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ከአለም የምግብ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ዴቪድ ቤስሊ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም አምባሳደር ሬድዋን የሰብዓዊ ጉዳዮችን ጨምሮ በኢትዮጵያ ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ ለዋና ዳይሬክተሩ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

አሸባሪው ህወሐት የነዳጅ እጥረት አጋጥሞኛል በሚል ለሚያቀርበው ክስ አምባሳደር ሬድዋን ÷ባለፈው ሳምንት 137 ሺህ 913 ሊትር ነዳጅ የጫኑ ሶስት ተሸከርካሪዎች መቀሌ መድረሳቸውን እና ይህም ለሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦት እንቅስቃሴ በቂ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት ለትግራይ ክልል የነዳጅና የጥሬ ገንዘብ አቅርቦትን ጨምሮ የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦቶች እንዲፋጠኑ ቁርጠኛ መሆኑንም ጠቁመዋል።

አምባሳደር ሬድዋን ከትናንት ጀምሮ ህወሐት በመቀሌ አውሮፕላን ማረፊያ የሰብዓዊ ድጋፍ የጫኑ አውሮፕላኖች እንዳያርፉ በመከልከል ወደ ትግራይ ክልል የሚደርሰውን ሰብዓዊ አቅርቦት እያደናቀፈ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ዴቪድ ቤስሊ በበኩላቸው÷ በቅርቡ በኢትዮጵያ ያደረጉትን ጉብኝት በማስታወስ÷ የፌደራል መንግስት ባደረገው ድጋፍ በትግራይ ያለው የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት መሻሻሉን ገልፀዋል፡፡

የዓለም የምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ በግጭት እና በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች የሰብዓዊ ድጋፍ ለማጠናከር በትጋት እየሰራ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ሁለቱ ወገኖች በትግራይ ክልል የነዳጅ አቅርቦት እና የሰብአዊ ዕርዳታ ለማድረግና በሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች በተከሰቱ ግጭቶችና በድርቅ የተጎዱ ወገኖችን ለመደገፍ በቅርበት ለመስራት መስማማታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.