Fana: At a Speed of Life!

የዘመን ባንክ አክሲዮን ማህበር አዳዲስ አሰራሮችን ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 7 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)  የዘመን ባንክ አክሲዮን ማህበር አዳዲስ አሰራሮችን ይፋ አደረገ

ባንኩ የማስተር ፕላቲኒየም ካርድ እንዲሁም የሞባይልና ኢንተርኔት መተግበሪያውን በአዲስ መልኩ ማዘጋጀቱን አስታዉቋል ።

የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ደረጀ ዘበነ÷ አዳዲስ እና የተሻሻሉ ቴክኖሎጂዎችን በማስተዋወቂያ መርሀ ግብር ላይ ተገኝተው  መልዕክት አስተላልፈዋል።

አገልግሎቶቹ  የጉዞ ቅድመ ክፍያ ካርድ እና የኤቲ ኤም የግብይት መፈፀሚያ ማሽኖችን የካርድ ንክኪን የሚያስቀር አገልግሎት መስጠት እንዲቻል የሚያግዙ ናቸው ተብሏል።

የሞባይልና ኢንተርኔት መተግበሪያው በአዲስ መልኩ መዘጋጀቱም ዘመኑ የደረሰበትን የቴክኖሎጂ ደረጃ ተጠቅሞ ለደንበኞች ቀልጣፋ፣ ተደራሽና ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠት እንደሚያስችል አንስተዋል።

ዋና ስራ አስፈጻሚው አክለውም ባንኩ በአውሮፓውያኑ በ2008 ዓ.ም በአንድ ቅርንጫፍ መስኮት አገልግሎት በመስጠት  ስራ ሲጀምር አንግቦ ከተነሳባቸው አላማዎች መካከልም የተቀላጠፈ የደንበኞች አገልግሎት ዘመኑን በሚመጥን የቴክኖሎጂ ድጋፍ መስጠትን መርህ በማድረግ  በመሆኑን ገልጸዋል።

ይህንን ተግባራዊ ለማድረግም ላለፋት አስራ ሶስት ዓመታት ከጊዜ ወደ ጊዜ አሰራሮቹን ለማሻሻል በትኩረት ሲሰራ መቆየቱን በማንሳት በዛሬው እለት ይፋ የተደረጉ አዳዲስ አሰራሮችም የዚሁ ስራ ማሳያ ናቸው ብለዋል።

ባንኩ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ እና ይበልጥ ለደንበኞች ለመቅረብ በሰራው ስራም ዛሬ ላይ የቅርንጫፍ ቁጥሩን በማስፋት   በመላው የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ 60 ቅርንጫፎችን በመክፈት የተሻለ የባንክ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን አስታውቋል ።

በትዝታ ደሳለኝ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.