Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ ከኮቪድ19 ጋር በተያያዘ ራሳቸውን አገለሉ

አዲስ አበባ ፣ጥቅምት 18 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ ከኮቪድ19 ጋር በተያያዘ ራሳቸውን ማግለላቸውን የፕሬዚዳንቱ ፅህፈት ቤት አስታወቀ።

ፕሬዚዳንቱ ቅዳሜ ምሽት በታደሙበት የእራት ግብዣ ላይ የተገኘ ሌላ እንግዳ በኮቪድ-19 መያዙ መረጋገጡን ተከትሎ ራሳቸውን አግልለዋል።

ጆሃንስበርግ ከተማ በሚገኝ ሆቴል በተዘጋጀው በእራት ግብዣው ላይ ከ35 በላይ ሰዎች ተገኝተው ነበር ነው የተባለው።

ይሁን እንጅ ፕሬዚዳንቱ የቫይረሱን ምልክት አለማሳየታቸው ተነግሯል።

ነገር ግን የጤና ባለሙያዎችን ምክረ ሃሳብ በመከተል ምልክት የሚያሳዩ ከሆነ ምርምራ ያደርጋሉም ነው የተባለው።

ፕሬዚዳንቱ ሥራቸውን ባሉበት ሆነው እንዲሚያከናውኑም ነው የተገለጸው።

በእራት ግብዣው ላይ የተገኙ እንግዶች ስለጉዳዩ እንዲያውቁ ተደርጓል፡፡

ምንጭ፡-ቢቢሲ

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.