Fana: At a Speed of Life!

የጅቡቲ ውሃ ፕሮጀክት የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ የመጀመሪያ ምዕራፍ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ ፣ጥቅምት 12 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሁለት ምዕራፍ ተከፍሎ እየተከናወነ የሚገኘው የጅቡቲ ውሃ ፕሮጀክት የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመር ዝርጋታ የመጀመሪያ ምዕራፍ መጠናቀቁ ተገልጿል፡፡

የውሃ ፕሮጀክቱ በሶማሌ ክልል አዲጋላና ኩለን ከተሞች መካከል የተገነባ ሲሆን÷ 28 ጉድጓዶች እና ሁለት የውሃ ማጠራቀሚ ፓምፕ ጣቢያዎች አሉት ተብሏል፡፡

የተዘረጋው የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመር ስምንት ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ሃይል የሚጠቀም መሆኑ ተገልጿል።

የፕሮጀክቱ ዋና ዓላማ የሁለቱን ሃገራት ህዝቦች የእርስ በእርስ ግንኙነት ለማጠናከር፣ የጅቡቲ ህዝቦችን የንፁህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ለማድረግ እና ከሃይል ሽያጭ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ መሆኑም ነው የተገለጸው፡፡

የፕሮጀክቱ አጠቃላይ ወጪ 49 ሚሊየን ብር መሆኑን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የተዘረጋው የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመር ጥራቱን የጠበቀና የጅቡቲን ህዝቦች የንፁህ መጠጥ ውሃ ችግር በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችል ሲሆን÷ የፕሮጀክቱ ሁለተኛ ምዕራፍ በቀጣይ የሚከናወን ይሆናልም ነው የተባለው፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ የድሬዳዋ አስተዳደር ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ፓርክ የ12 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ጥንድ 33 ኪሎ ቮልት የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመር መዘርጋቱ ተገልጿል፡፡

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.