Fana: At a Speed of Life!

የገልፍ የምግብ ኤክስፖ ኢትዮጵያ የውጪ ምርቶቿን እንድታስተዋውቅ እድል ፈጥሯል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በዱባይ ገልፍ የምግብ ኤክስፖ መሳተፏ የውጪ ምርቶቿን እንድታስተዋውቅ እድል መፍጠሩን የውጭ ንግድ እና ፕሮሞሽን ዘርፍ ሚኒስቴር ዲኤታ አቶ ዳንጌ ቦሩ ገለፁ፡፡
 
በዱባይ ወርልድ ትሬድ ሴንተር በተካሄደዉ ገልፍ ፉድ ኤክስፖ ኢትዮጵያ የተለያዩ የምግብ ምርቶችን አቅርባለች፡፡
 
በኤክስፖው ላይ የተገኙት በንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የውጭ ንግድ እና ፕሮሞሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ዳንጌ ቦሩ እንደተናገሩት፥ ኢትዮጵያ በርካታ አለም ዓቀፋዊ ድርጅቶች በአንድ ጣራ ስር በተገኙበት የምግብ ኤክስፖ ላይ መሳተፏ ሀገሪቱ ያሏትን የወጪ ምርቶች ለማስተዋወቅ አድል ፈጥሯል ብለዋል፡፡
 
ኢትዮጵያ በጥራጥሬ እና ቅባት እህሎች፣ በቡና እና በቅመማ ቅመም፣ በማር እና በስጋ እንዲሁም በቁም እንስሳት ምርቶች ከፍተኛ አቅም አላት ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው፥ የዱባዩ የምግብ ኤክስፖ በዘርፉ ላይ ከሚሰሩ አለም አቀፍ ኩባንያዎች ጋር ተቀራርቦ ለመስራት አድል የፈጠረ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡
 
በእለቱም በተለያዩ የወጪ ምርቶች ላይ ከኢትዮጵያ ጋር የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት አብሮ ለመስራት ስምምነት ማድረጋቸውን ሚኒስትር ዴኤታዉ ተናግረዋል፡፡
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.