Fana: At a Speed of Life!

የግብፅ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ሆስኒ ሙባረክ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 17፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የግብፅ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ሆስኒ ሙባረክ በ91 ዓመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለዩ።

በፈረንጆቹ 2011 በህዝባዊ አመፅ ከስልጣን የተወገዱት የቀድሞው ፕሬዚዳንት ሀገሪቷን ለ30 ዓመታት መርተዋል።

የሀገሪቱ መንግስት ቴሌቪዥን እንደዘገበው ሆስኒ ሙባሪክ የቀዶ ህክምና ከተደረገላቸው ከሳምንታት በኋላ ህይወታቸው አልፏል።

የግብፅ አራተኛው ፕሬዚዳንት የነበሩት ሆስኒ ሙባራክ በአረብ አብዮት ከስልጣን እስከተወገዱበት ጊዜ ድረስ ሀገሪቷን መርተዋል።

በፈረንጆቹ 2011 ከስልጣን ከተነሱ በኋላ እስር ላይ የነበሩ ሲሆን በ2017 ከቀረበባቸው ክስ ነፃ መሆናቸውን ተከትሎ ከእርስ መፈታታቸው ይታወሳል።

በ1928 በናይል ዴልታ ገጠራማ አከባቢ የተወለዱት ሆስኒ ሙባረክ የአገዛዝ ዘመናቸው በሙስና ፣ በፖሊስ ጭካኔ ፣ በፖለቲካ ጭቆና እና በኢኮኖሚያዊ ችግሮች ወቀሳ ይቀርብበተዋል
ምንጭ፡- አልጀዚራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.