Fana: At a Speed of Life!

ዩዌሪ ሙሴቬኒ በኡጋንዳ የተካሄደውን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ማሸነፋቸው ተረጋገጠ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኡጋንዳ የተካሄደውን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ዩዌሪ ሙሴቬኒ ማሸነፋቸው የሀገሪቱ ምርጫ ኮሚሽን ይፋ አደረገ።

ይህም ባለፉት 35 ዓመታት ኡጋንዳን የመሩት የ75 ዓመቱ ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ለቀጣዩቹ አምስት አመታት ሀገሪቱን ይመራሉ።

የፕሬዚዳንቱ ዋነኛ ተቀናቃኝ ቦቢ ዋይን ምርጫው የተጨበረበረ መሆኑን በመግለፅ ዜጎች ውጤቱን ውድቅ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል።

ዩዌሪ ሙሴቬኒ 5 ነጥብ 85 ሚሊየን ድምፅ ወይንም 58 ነጥብ 6 በመቶ ማግኘታቸውን የሀገሪቱ ምርጫ ኮሚሽን ይፋ አድርጓል።

በተመሳሳይ ቦቢ ዋይን 3 ነጥብ 48 ሚሊየን ወይንም 34 ነጥብ 8 በመቶ ማግኘቱ ነው የተገለፀው።

በኡጋንዳ ዋና ከተማ ካምፓላ የፀጥታ ሀይሎች እና ፖሊሶች  ቅኝት እያደረጉ መሆኑን አልጀዚራ በዘገባው ላይ አስፍሯል።

የ38 ዓመቱ ቦቢ ዋይን በኡጋንዳ በወጣቶች ጠንካራ ድጋፍ እንዳለው የሚነገር ሲሆን በሀገሪቱ ለውጥ እንዲመጣ እንዲሁም  የአምባገነንነት እና የሙስና ዘመን የሚለው የፕሬዚዳንቱ ዘመን እንዲያበቃ ጥሪ አቅርቧል።

በሀገሪቱ ምርጫው ከመካሄዱ አንድ ቀን በፊት መንግስት ኢንተርኔት የዘጋ ሲሆን አሁንም ኢንተርኔቱ እንዳልተለቀቀ ዘገባው አመልክቷል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.