Fana: At a Speed of Life!

ያልተመጣጠነ አመጋገብ እና የአየር ንብረት ለውጥ በህጻናት ላይ ስጋት ደቅኗል – ተመድ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 11 ፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) የንጥረ ምግብ አቅርቦት እጥረት እና የአየር ንብረት ለውጥ በሁሉም ሕፃናት ላይ ስጋት መደቀኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ።

ከተመድ፣ ከዓለም ጤና ድርጅት እና ላንሴት ሜዲካል ጆርናል የተውጣጣ ቡድን በጋራ ባወጣው ሪፖርት የስነ ምህዳር መዛባት፣ የአየር ንብረት ለውጥ፣ ያልተመጣጠነ አመጋገብ እና ስደት ዓለም ላይ ባሉ ህጻናት ላይ ከፍተኛ ስጋት ደቅኗል ሲል አስጠንቅቋል።

180 ሃገራትን የዳሰሰው ሪፖርት ከላይ የተጠቀሱት ሁኔታዎች የህጻናት ስጋት መሆናቸውንም ይገልጻል።

ባለፉት አራት አስርት አመታት ውስጥ በህጻናት ላይ የሚከሰት ከልክ በላይ ውፍረትን ጨምሮ የአልኮል መጠጦች፣ ፈጣን ምግቦች እና ስኳር የበዛባቸው ጣፋጭ መጠጥ ማስታወቂያዎች በስፋት ወደ ህጻናት ተዳርሰዋልም ነው ያለው።

ሪፖርቱ በመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ፣ በቻድ፣ በሶማሊያ፣ በኒጀር እና በማሊ የሚገኙ ህጻናት በከፍተኛ መጠን ተጋላጭ መሆናቸውንም አመላክቷል።

በተቃራኒው ደግሞ በኖርዌይ፣ ደቡብ ኮሪያ እና በኔዘርላንድስ የሚገኙ ህጻናት ከስጋቱ ነጻና የተሻለ ህይዎት ያላቸው ናቸው ተብሏል።

ቡድኑን በሊቀ መንበርነት የመሩት ሴኔጋሊዊቷ አዋ ኮል ሴክ ደግሞ፥ አንዳንድ ድሃ ሃገራት ዝቅተኛ የካርበን ዳይ ኦክሳይድ ልቀት ቢኖራቸውም፥ በርካታ ህጻናት በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ በከፍተኛ ሁኔታ እየተጎዱ ነው ብለዋል።

በለንደን ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ በሚገኘው ግሎባል ሄልዝ ዳይሬክተር የሆኑት እና በዓለም አቀፉ የህጻናት ጤና ተቋም በተመራማሪነት የሚሰሩት ፕሮፌሰር አንቶኒ ካስቴሎ በበኩላቸው፥ አሁንም ሆነ ወደፊት የህጻናትን ጤንነት የሚጠብቅ ሃገር አለመኖሩ ትልቁ መልዕክት መሆኑን ጠቅሰዋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.