Fana: At a Speed of Life!

ደቡብ ኮሪያ ከኒውክሌር የበለጠ አቅም ያለው ሚሳኤል እያበለጸገች መሆኑ ተሰማ

አዲስ አባባ፣ ነሐሴ 28፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ደቡብ ኮሪያ ከኒውክሌር ጦር የተሻለ አቅም ያለው ሚሳኤል እያበለጸገች መሆኑ ተሰምቷል፡፡

አዲሱ ሚሳኤል ከምድር በታች የተቀበሩ የጦር መሳሪያዎችን የማውደም አቅም እንዲኖረው ተደርጎ የተሰራ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡

ሚሳኤሉ ከ350 እስከ 400 ኪሎ ሜትር የመምዘግዘግ አቅም ያለው ሲሆን÷ይህም የባላንጣዋን ሰሜን ኮሪያ ሁሉንም አካባቢዎች መድረስ የሚችል መሆኑ ተመላክቷል፡፡

አሁን ላይ ሚሳኤሉን የማበልጸጉ ሂደት የመጨረሻ ደረጃ ላይ የሚገኝ መሆኑን ዮንሃፕ የተሰኘው የሀገሪቱ ዜና ወኪል ዘግቧል፡፡

ደቡብ ኮሪያ ዘመኑን የዋጀ የጦር መሳሪያ ማበልጸጓን አጠናክራ እንደምትቀጥልም አልጀዚራ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.