Fana: At a Speed of Life!

ዲሽቃ በመስራት ወራሪ ጠላትን ለማጥፋት በፈጠራ ስራ የታገዘው የጠለምት ወጣቶች ተጋድሎ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪውን ህወሓት ለመደምሰስ ዲሽቃ የተሰኘውን የጦር መሳሪያ በመስራት በፈጠራ ስራ የታገዙት የጠለምት ወጣቶች ለሌሎችም አርአያ የሚሆን ተተጋድ ነው የፈጸሙት፡
 
አሸባሪው እና ወራሪው የህወሓት ቡድን በአማራ እና አፋር ክልሎች በወረራ ይዟቸው በነበሩ አካባቢዎች ላይ ለመስማት የሚዘገንን ሰብዓዊ እና ቁሳቂ ጉዳት አድርሷል፡፡
 
አሸበሪ ቡድኑን ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ በመደምሰስ የጠነሰሰውን ሀገር የማፍረስና ህዝብ የመጨረስ ሴራ ለማክሸፍም ሁሉም የጸጥታ ሃይሎች ከየአካባቢው ህብረተሰብ ጋር በመቀናጀት አስፈላጊውን እርምጃ በመውሰድ ለይ ናቸው፡፡
 
የጠለምት ወረዳ ወጣቶችም አሸባሪውን የህወሓትን ወራሪ ሃይል ለማጥፋት በሚደረገው የህልውና ትግል ላይ የበኩላቸውን ድርሻ በመወጣት ላይ ይገኛሉ፡፡
 
ወጣቶቹ ያለማንም እገዛ የራሳቸውን የፈጠራ ውጤት ተጠቅመው ከርቀት ጠላትን የሚመታ ዲሽቃ የተሰኘውን የጦር መሳሪያ አዘጋጅተው የጠላትን ቅስም ሰብረዋል፡፡
 
በጦር መሳሪያው በመታገዝም ከወረዳቸው አሸባሪው ቡድኑን አስወጥተዋል፤ በርካታ የስብር ቡድኑን አባላት በመደምሰስም ደማቅ ታሪካቸውን ጽፈዋል፡፡
 
የፈጠራ ባለቤቶቹ ወጣት ሹመት አስማረ እና ወጣት ግርማው ከፍያለው ይባላሉ፡፡ ወጣት ሹመት አስማረ በሙያው መካኒክ መሆኑን ይናገራል፣ በሚሊሻ ሰልጥኖ አሁን ለይ በጠለምት ፋኖ ውስጥ መደራጀቱን ነው የሚገልጸው፡፡
 
“ጠላት አካባቢያችንን ለመውረር አሰፍስፎ ነበር፤ ከሩቅም ይታየን ነበር፤ በዚህ የጭንቅ ወቀትም ጠላትን እንዴት አድርገን ነው ከሩቅ መምታትና መግደል የምንችለው? ስል ለራሴ ጥያቄ አቀረብኩ” ይላል ወጣቱ የፈጠራ ባለሙያ፡፡
 
በዚህ ሃሳብ ላይ እያለ ድንገት የዲሽቃ ጥይት ማግኘቱን የሚናገረው ወጣቱ ÷ የጦር መሳሪያውን እንዴት መስራት እንዳሚቻል ከጓደኛው ጋር መመካከራል፡፡
 
በአሰራር ሂደቱ ላይ አስፈላጊውን መረጃ ከሰበሰቡ በኋላ የጦር መሳሪያውን ከብረት የተሰራ የውሃ ቱቦ እና ሌሎች ግብዓቶችን በመጠቅም እንደሰሩት ይናገራል፡፡
 
በሰሩት የዲሽቃ የጦር መሳሪያ ላይ አስፈላጊውን ሙከራ በማድረግም እቅዳቸውን እውን ማድረግ እንደቻሉ ነው ያስረዳው።
 
የጦር መሳሪያው በ3 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ጠላትን አልሞ የመምታት አቅም እንዳለውም ወጣቶቹ ይናገራሉ፡፡
 
የጦር መሳሪያው ጠላት በተጠጋ ወቅት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳደረገላቸው የሚናገሩት ወጣቶቹ÷ በተለይም የሽብር ቡድኑ አባላት ዲሽቃ አላቸው በሚል በቅርበት ሊዳፈሩን አልቻሉም ይላሉ፡፡
 
በወቅቱም በግንባሩ የሚገኘው የጠለምት ብርጌድ በዚህ የዲሽቃ ጦር መሳሪያ ታግዞ ጠላትን አይቀጡ ቅጣት መቅጣቱን ያወሳሉ፡፡
 
ለመጀመሪያ ጊዜ በሰሩት ዲሽቃ ጥሩ ውጤት ማስመዝገባቸውን የሚናገሩት ወጣቶቹ ÷ በቀጣይ የጦር መሳሪያውን በተሻለ ሁኔታ ለመስራት እንደሚፈልጉ መናገራቸውን ከሰሜን ጎንደር ዞን ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ወደ ፊትም መሳሪያውን ጥራት እና ብዛት ባለው መልኩ በመስራት ወራሪው የህወሓት ሽብር ቡድን ለአካባቢያቸው ብሎም ለኢትዮጵያ ስጋት እንዳይሆን ለማድረግ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እንሰራለን ነው ያሉት፡፡
 
ለዚህም መንግስት ሊያበረታታንና ሊደግፈን ይገባል የሚሉት ወጣቶቹ÷ የሽብር ቡድኑን በዘላቂነት ለመደምስሰስ መከላከያ ሰራዊትን ተቀላቅለው በቂ ስልጠና የመውሰድ ፍላጎት እንዳላቸውም ተናግረዋል፡፡
 
አሁን ላይ የሽብር ቡድኑን በአጭር ጊዜ ለመደምስ እና በቀጣም የኢትዮጵያ ስጋት እንዳይሆን ለማድረግ ወጣቱ በመደራጀት አካባቢውን በንቃት ከመጠበቅ ባለፈ መከላከያ ሰራዊትን መቀላቀል እንዳለበት ወጣቶቹ መክረዋል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.