Fana: At a Speed of Life!

ዶናልድ ትራምፕ ሽንፈታቸውን አምነው መቀበላቸው ተሰምቷል

አዲስ አበባ፣ ህዳር 15፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ዶናልድ ትራምፕ በፕሬዚዳንታዊ ምርጫ መሸነፋቸውን አምነው ተቀበሉ፡፡

ትራምፕ በምርጫው አልተሸነፍኩም ሲሉ ቢቆዩም በመጨረሻ የተመራጩን ጆ ባይደንአሸናፊነት አምነው ተቀብለዋል ነው የተባለው፡፡

የሃገሪቱ ጠቅላላ አገልግሎት አስተዳደር ጆ ባይደንን አሸናፊ ናቸው በማለት እውቅና መስጠቱም ተነግሯል ፡፡

በሚቺጋን ግዛት የባይደን አሸናፊነት ይፋ መሆንን ተከትሎ አዲሱ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት መሆናቸው ተረጋግጧልም ተብሏል፡፡

ፔንታጎንም ለባይደን አስተዳደር የህዝቡን ተስፋ ባገናዘበ መንገድ ሙያዊ እና ለብሔራዊ ደህንነት ያለውን ቁርጠኝነት በሚመጥን መልኩ ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.