Fana: At a Speed of Life!

ጉዳት የደረሰባቸው የጤና ተቋማት አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ የ43 ሚሊየን ብር ኘሮጀክት ተዘጋጀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ፣ በአፋር እና በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች በአሸባሪው ህወሃት ወረራና ተከስቶ በነበረው ግጭት ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው የጤና ተቋማት ተጠናክረው አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ የ43 ሚሊየን ብር ኘሮጀክት ማስጀመሪያ መርሀ ግብር ተካሄደ።
ፕሮጀክቱ በኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ማህበር፣ በጤና ሚኒስቴር እና በሌሎች አጋር አካላት የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል።
በሒልተን ሆቴል በተካሄደው በዚሁ መርሀ ግብር ላይ÷ የጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ማህበር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እና የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል፡፡
በመርሃሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የጤና ሚንስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ÷ በሽብር ቡድኑ ህወሓት የወደሙ የጤና ተቋማትን መልሶ ለመገንባት የመንግስት ብቻ መሆን የለበትም፤ አጋር ድርጅቶችም ንቁ ተሳትፎ ማድረግ አለባቸው ብለዋል፡፡
 
በቅድስት አባተ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.