Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ኢትዮጵያ ለወንጀለኛ ቦታ የላትም አሉ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ኢትዮጵያ ለወንጀለኛ ቦታ የላትም አሉ፡፡
 
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስተላለፉት የትዊተር መልዕክታቸው የትግራይ ሕዝብ ሆነ ማንኛውም ዜጋ የወንጀለኞች መሸሸጊያ አይሆንም ብለዋል፡፡
 
አንቀጽ 51 በመጥቀስም የፌደራል መንግስቱ ህገመንግስቱን ያስከብራል ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፡፡
 
እንዲሁም መከላከያ ሰራዊቱ ላይ ጥቃት በፈጸመው ቡድን ላይ የህግ የበላይነትን ለማስከበር እርምጃዎችንም ይወስዳል ብለዋል፡፡
 
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመጨረሻም ወንጀል የፈጸሙ አካላትን ከተሸሸጉበት በማውጣት መላው የሃገሪቱ ህዝብ ወደ ብልጽግና ጎዳና እንመራለን ብለዋል በመልዕክታቸው፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.