Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ አስመራ ገቡ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለሁለት ቀናት የስራ ጉብኝት አስመራ ገብተዋል፡፡
ሁለቱ መሪዎች በሁለትዮሽና በቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እና የልዑካን ቡድናቸው አስመራ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ደማቅ አቀባበል እንደተደረገላቸው የኤርትራው የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል በቲውተር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል።
በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተመራው ቡድን የመከላከያ ሚኒስትሩን ዶክተር ቀናዓ ያደታ እና የኢኖቬሽንና የቴክኖሎጂ ሚኒስትሩን ዶክተር አብርሃም በላይን ማካተቱ ተገልጿል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-

https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.