Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅና የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ለማጠናከር ቃል ገቡ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 15 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የኢትዮጵያ እና የቻይና 50ኛ አመት የዲፕሎማቲክ ግንኙነትን በተመለከተ ከቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ተለዋውጠዋል።

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ባለፉት 50 ዓመታት ኢትዮጵያ እና ቻይና ጠንካራ ግንኙነት መፍጠራቸውን በመግለፅ በምክክር የጋራ የፖለቲካ መተማመን እና ፍሬያማ ትብብር መፍጠራቸውን ገልፀዋል።

ግንኙነቱ ወደ ሁሉን አቀፍ ስትራቴጂክ ትብብር ማደጉ የሀገራቱ ግንኙነት የበለጠ እንዲጠናከር እና ለሀገራቱ ህዝቦች የጋራ ተጠቃሚነት በበርካታ ዘርፎች ትብብሮች እንዲፈጠር መንገድ መክፈቱንም ፕሬዚዳንቷ ጠቁመዋል።

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ከቻይናው ፕሬዚዳንት ጋር በነበራቸው ቆይታ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ለማጠናከር በቅርበት እንደሚሰሩ ገልፀዋል።

የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ በበኩላቸው የሀገራቱ ግንኙነት ለረጅም ዘመን የዘለቀ መሆኑን በመግለፅ አሁንም የበለጠ እየጠነከረ መሆኑን አውስተዋል።

የተመሰረተው ሁሉን አቀፍ ስትራቴጂክ ትብብር ግንኙነት በመተማመን ላይ የተመሰረተ ፖለቲካዊ ግንኙነት እንዲጠናከር ማድረጉንም ገልፀዋል።

ስኬታማ ዘርፈብዙ ትብብር እና በዋና የሀገራቱ ፍላጎቶች ላይም የጋራ መግባባት እና ድጋፍ እንዲፈጠር አድርጓል ማለታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.