Fana: At a Speed of Life!

125ኛው የአድዋ ድል በዓል በተለያዩ ሃገራት በሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች ተከበረ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 22 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 125ኛው የአድዋ ድል በዓል በተለያዩ ሃገራት በሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች በተለያዩ ዝግጅቶች ተከበረ፡፡

በዓሉ የአድዋን ድል በሚዘክሩ ዝግጅቶች እንዲሁም ጥናታዊ ጽሁፎችን በማቅረብ ተከብሯል፡፡

በዚህም በኬኒያ፣ ጂቡቲ፣ ታንዛኒያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ጀርመን፣ ኳታር፣ ጣሊያንን ጨምሮ በቻይና እና ሌሎች ሃገራት እና ሌሎች ኤምባሲዎች ተከብሯል፡፡

ኤምባሲዎቹ በበይነመረብ እና በሌሎች መገናኛ ዘዴዎች ከኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም ከተለያዩ የኢትዮጵያ ወዳጆች ጋር ድሉን መዘከራቸው ነው የተገለጸው፡፡

በኬኒያ በተከበረው በዓል ላይ ጥናታዊ ጽሁፋቸውን ያቀረቡት ፕሮፌሰር ማሞ አፍሪካውያን አንድነታቸውን ማጠናከር እንደሚገባቸው ገልጸዋል፡፡

የአፍሪካ ሕብረት “የአድዋ ድል የመላው አፍሪካ አንድነት ቀን” መሆኑን እውቅና እንዲሰጥም ምክረ-ሃሳብ አቅርበዋል፡፡

የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስትር ፕሮፌሰር ሂሩት ካሳው በበዓሉ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት አድዋ በጥቁር ህዝቦች በነጮች ላይ የተመዘገበ አንፀባራቂ ድል እና የነጮች የበላይነት አስተሳሰብ የተመሰረተበት መሠረት የተናደበት ነበር ብለዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.