Fana: At a Speed of Life!

39ኛው የአፍሪካ የአስፈጻሚ ምክር ቤት ስብሳባ የኢትዮጵያን ገፅታ ለማስተዋወቅ ጉልህ ሚና አለው- የውጭ ጉዳይ ሚኒ/ር

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፕሮቶኮል ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀነራል ፈይሰል አሊይ በአዲስ አበባ ነገ የሚጀመረውን 39ኛው የአፍሪካ የአስፈጻሚ ምክር ቤት ስብሰባን አስመልከተው ገለጻ አድርገዋል፡፡
የአፍሪካ ህብረት የአስፈጻሚ ምክር ቤት ጉባኤን ለማካሄድ በቂ ዝግጅት መደረጉን ጠቅሰው ÷ ጉባኤው በኢትዮጵያ መካሄዱ አገሪቷ ለአፍሪካ አጀንዳ ስኬት ያላትን ቀዳሚ ቦታ እና ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑን ጠቅሰዋል።
ኢትጵያ ሁሌም የአፍሪካ አጀንዳ እንዲሳካ ቁርጠኛ አቋም ያላት መሆኗን ጠቁመው÷ ይህንኑ ጥረቷን አጠናክራ ትቀጥላለችም ብለዋል፡፡
39ኛው የአፍሪካ የአስፈጻሚ ምክር ቤት ስብሳባ ከጉዳዩ ክንውን በተጓዳኝ የኢትዮጵያን ገፅታ ለማስተዋወቅ ጉልህ ሚና አለው ብለዋል።
ኢትዮጵያ አፍሪካዊያን የራሳቸውን የውስጥ ጉዳይ በራሳቸው እንዲፈቱ በግንባር ቀደምትነት ስትንቀሳቀስ እንደነበር አስታውሰው÷ ምንጊዜም በአፍሪካ ጉዳይ ግንባር ቀደም ሚናዋን መወጣቷን ትቀጥላለች ነው ያሉት።
ኢትዮጵያ ከአፍሪካዊያን ወንድሞች ጋር ያላትን ረጅም ጊዜ የትብብር ግንኙነት የምታጠናክርበት አንዱ መንገድ መሆኑንም ጠቁመዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ለሁለት ቀናት በአዲስ አበባ ለሚካሄደው 39ኛው የአፍሪካ የአስፈጻሚ ምክር ቤት ስብሰባ በቂ ዝግጅት መደረጉንም ተናግረዋል።
በስብሰባው የ34 የአፍሪካ አገራት ሚኒስትሮች ይሳተፋሉ፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.