Fana: At a Speed of Life!

6ኛው ሃገራዊ ምርጫ ሰላማዊና ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ አስፈላጊው ዝግጀት መደረጉ ተገለፀ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 7፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ሃገራዊው ምርጫ በሰላም እንዲጠናቀቅ የፌዴራል እና የክልል የደህንነትና የፀጥታ መዋቅር በቂ ዝግጅት ማድረጋቸውን የብሔራዊ ደህንነትና መረጃ አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ተመስገን ጥሩነህ ተናገሩ።
የፌዴራል እና የክልል የደህንነት እና የፀጥታ አካላት ግብረሐይል ወቅታዊ የሀገሪቷን ደህንነት የሚገመግም እና ቀጣይ አቅጣጫዎችን የሚያስቀምጥ ውይይት እያደረጉ ነው።
በዚሁ ወቅት የብሔራዊ ደህንነት እና መረጃ አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ተመስገን ጥሩነህ ቀጣዩ የምርጫ እና ድህረ ምርጫ ሰላማዊ እንዲሆን በቂ ዝግጅት እንደተደረገ መናገራቸውን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡
ምርጫውን እና የግድቡን ሙሌት ለማስተጓጎል የሚሰሩ የውጭ እና የውስጥ ጠላቶች መኖራቸውን የተናገሩት አቶ ተመስገን ከደህንነት መስሪያ ቤቱ ክትትል አያመልጡም ብለዋል።
የፌዴራል እና የክልል የፀጥታ እና ደህንነት አካላት የጋራ ግብረ ሀይልም የሀገሪቷን ወቅታዊ የደህንነት ሁኔታ በመገምገም ቀጣይ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.