Fana: At a Speed of Life!

7ኛው የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ሥነ ሥርዓት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) 7ኛው ዙር የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ሥነ ሥርዓት ተካሂዷል።

ብሔራዊ የጥራት ሽልማት ሥነ ሥርዓቱ በዛሬው ዕለት ነው በብሔራዊ በቤተ መንግሥት የተካሄደው።

በሽልማት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ባለሥልጣናት፣ የተለያዩ ድርጅቶች ተወካዮች፣ ተጋባዥ እንግዶችና የተወዳዳሪ ድርጅቶች ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

በስነ ሥርዓቱ ላይ አምራች፣ ለትርፍ የተቋቋሙ አገልግሎት ሰጪ ፣ ለትርፍ ያልተቋቋሙ አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች እና በኮንስትራክሽን ዘርፎች የተሰማሩ ተቋማት ተወዳድረው ተሸላሚ ሆነዋል።

በመድረኩ ላይ የባህርዳሩ ጋምቢ አጠቃላይ ሆስፒታል እና ሀረር ቢራ አክሲዮን ማህበር በከፍተኛ ውጤት የጥራት ሽልማት ተሸላሚዎች በመሆን ሽልማታቸውን ከፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ እጅ ተቀብለዋል።

በመድረኩ ላይ ሌሎች ተቋማትም ባመጡት ደረጃ መሰረት በመድረኩ ላይ ተገኝተው ሽልማታቸውን ተቀብለዋል።

የሽልማት ድርጅቱ ከተመሰረተበት 2000 ዓ.ም አንስቶ በሀገር አቀፍ ደረጃ በሃገር ውስጥ ከሚንቀሳቀሱ አምራቾች፣ አገልግሎት ሰጪዎች፣ የኮንስትራክሽን ድርጅቶች እና ተቋማትን በጥራት አወዳድሮ በመሸለም እውቅና ሲሰጥ መቆየቱ ይታወቃል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.