ሲዳማ ቡና ወንድማገኝ ተሾመን ዋና አሰልጣኝ አድርጎ ሾመ
አዲስ አበባ፣ሐምሌ 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሲዳማ ቡና በጊዜያዊ አሰልጣኝነት ክለቡን ሲመራ የነበረውን ወንድማገኝ ተሾመን በዋና አሰልጣኝነት መሾሙን አስታወቀ፡፡
ከረዳት ወደ ጊዜያዊ ዋና አሰልጣኝነት በመምጣት ክለቡ በደረጃ ሰንጠረዡ ሦስተኛ ላይ ተቀምጦ እንዲያጠናቅቅ ያስቻለው አሰልጣኝ ወንድማገኝ ተሾመ÷ ለቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት የሲዳማ ቡና ዋና አሰልጣኝ በመሆን መሾሙን ሶከር ኢትዮጵያ ዘግቧል፡፡
አሰልጣኝ ወንድማገኝ ተሾመ በተጫዋችነት ዘመኑ÷ የሲዳማ ቡና፣ ሀዋሳ ከተማ እና ሀድያ ሆሳዕና የግራ መስመር ተከላካይ እንደነበር ዘገባው አስታውሷል፡፡
ከዘንድሮው የውድድር ዓመት ጅማሮ አንስቶ ረዳት በስተመጨረሻም ጊዜያዊ አሰልጣኝ በመሆን ጥሩ ጊዜን በማሳለፉ ነው ዋና አሰልጣኝ ሆኖ የተሾመው፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!