ዋልያዎቹ ሁለተኛ የምድብ ጨዋታቸውን ዛሬ ከጊኒ ጋር ያደርጋሉ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሁለተኛ የምድብ ጨዋታውን ዛሬ ምሽት ከጊኒ አቻው ጋር ያደርጋል፡፡
ጨዋታው ዛሬ ምሽት 4፡00 ላይ በራባት ልዑል ሞውላይ አብደላ ስታዲየም ይደረጋል፡፡
አሰልጣኝ ውበቱ አባተ በሰጡት መግለጫ÷ ከሚሊዮን ሰለሞን ውጭ ሌሎች ተጫዋቾች በሙሉ ጤንነት እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡
ለጨዋታውም ዝግጁ መሆናቸውን አሰልጣኝ ውበቱ ማረጋገጣቸውን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
ብሔራዊ ቡድኑ ቀደም ሲል ባደረገው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ በጊኒ አቻው 2 ለ 0 መሸነፉ ይታወሳል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!