1 ሺህ 232 ኢትዮጵያውያን ከሳውዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳውዲ ዓረቢያ ችግር ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 232 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡
ከተመላሾች ውስጥ 1 ሺህ 231 ወንዶች፣ 1 ሴት እና ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ 12 ታዳጊዎች እንደሚገኙ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
ለተመላሽ ዜጎች በአውሮፕላን ማረፊያ እና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ሥራ እየተከናወነ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡