ከህንድ የመጡ 14 የህክምና ባለሙያዎች ነጻ የህክምና አገልገሎት እየሰጡ ነው
አዲስ አባባ፣ የካቲት 5፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከህንድ የመጡ 14 የህክምና ባለሙያዎች በኢትዮጵያ ነጻ የህክምና አገልገሎት እየሰጡ ነው።
በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚኒሊየም ሜዲካል ኮሌጅ የህክምና አገልግሎት ምክትል ፕሮቮስት ዶክተር ሊያ ተፈራ፥ ህክምናው የሚሰጠው በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚኒሊየም ሜዲካል ኮሌጅ የሜዲካልና በአቤት አጠቃላይ ሆስፒታል መሆኑን ገልፀዋል።
ከዶክተሮቹ ውስጥ ስምንቱ በተለያዩ የቀዶ ህክምና ዘርፍ የረጅም ጊዜ ልምድ ያላቸው ናቸው ተብሏል።
ሆስፒታሉ ከፖኒ ሂንዲያ ሮተሪ ክለብ ጋር በመተባበር ባገኘው ድጋፍ ህክምናው እንደሚሰጥም ዶክተር ሊያ ተናግረዋል።
ዶክተሮቹ በዋናነት የሆድ እቃ፣ የምግብ መተላለፊያ ቱቦዎች፣ የሽንትና የሽንት ቱቦ ችግርና በማህጸን ህመሞች ዙሪያ ህክምና እየሰጡ መሆኑንም አስረድተዋል።
ከአጥንትና ከመገጣጠሚያ አካላትጋር ለተያያዙ ችግሮችም ዶክተሮቹ በአቤት ሆስፒታል ህክምና እየሰጡ መሆኑንም ጠቁመዋል።
የቀዶ ህክምናው ካለፈው ሰኞ ጀምሮ እየተሰጠ ሲሆን እስከ ዓርብ ይቀጥላል ተብሏል።
እስካሁን በተደረገው የህክምና ሂደትም ከ30 በላይ ህሙማን የህክምና አገልግሎት ማግኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision