የምጣኔ ሃብት ምሁሩ ዘመዴነህ ንጋቱ ‘ጽዱ ኢትዮጵያ’ ንቅናቄን ተቀላቀሉ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የምጣኔ ሃብት ምሁሩ ዘመዴነህ ንጋቱ ‘ጽዱ ኢትዮጵያ’ ንቅናቄን መቀላቀላቸውን አስታወቁ።
የምጣኔ ሃብት ምሁሩ ዘመዴነህ ንጋቱ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይፋ የሆነው “ጽዱ ጎዳና- ኑሮ በጤና” ንቅናቄ ወቅቱ የሚፈልገው ድንቅ ኢኒሼቲቭ ነው ብለዋል።
ቤተሰቤ ንቅናቄውን ተቀላቅሏል በማለት ገልጸው፤ ሁሉም ወገን በዚህ ንቅናቄ እንዲሳተፍ አበረታታለሁ ሲሉ ጥሪ አስተላልፈዋል።
በርከት ያሉ የመጸዳጃ ቤቶች ለመገንባት በገንዘብ ድጋፍ ማድረግ ለሚፈልጉ ዜጎች በንግድ ባንክ አካውንት 1000623230248 እንዲሁም በብሔራዊ ባንክ ዶላር አካውንት 0101211300016 “ጽዱ ኢትዮጵያ” ማበርከት ይችላሉ።