Fana: At a Speed of Life!

በጅቡቲ እየተካሄደ ያለው ሄሪቴጅ ምክክር መድረክ ለአፍሪካ ቀንድ ትልቅ ጠቀሜታ ያለው ነው – አምባሳደር መሀሙድ ድሪር

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለ5ኛው ጊዜ በጅቡቲ እየተካሄደ ያለው ሄሪቴጅ ምክክር መድረክ በአጠቃላይ ለአፍሪካ ቀንድ ትልቅ ጠቀሜታ እንዳለው አምባሳደር መሀሙድ ድሪር ገለጹ፡፡

ለ5ኛ ጊዜ በዓለም አቀፉ ሄሪቴጅ ኢንስቲትዩት አዘጋጅነት በጅቡቲ ሪፐብሊክ ርዕሰ መዲና ጅቡቲ ከተማ እየተካሄደ ያለውና ከአፍሪካ ቀንድና ከሌሎች አህጉራት የተወጣጡ ምሁራን፣ ፖለቲከኞች፣ ተዋቂ ግለሰቦች፣ የሚሳተፉበት መድረክ ነው፡፡

ይህ መድረክ በአጠቃላይ ለአፍሪካ ቀንድ ህዝቦች ትልቅ ጠቀሜታ ያለው መድረክ መሆኑን በምክክሩ ላይ የተገኙት በኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኢጋድና አጎራባች አገራት ጉዳዮች ጄነራል ዳይሬክተሩ አምባሳደር መሀሙድ ድሪር ገልጸዋል፡፡

ፎረሙ በየዓመቱ የሚካሄድ ሲሆን፥ በሁሉም የአፍሪካ ቀንድ አገራት የተውጣጡ ምሁራን የሚገናኙበትና ለቀጠናው የጋራ ጥቅሞች እንዲሁም በአገራቱ የጋራ ጉዳዮች፣ ቀጠናዊና ዲፕሎማሲያዊ ትብብርን የሚወያዩበት አለም አቀፋዊ መድረክ ነው ብለዋል አምባሳደሩ፡፡

በተጨማሪም የምክክር መድረኩ ለቀጠናው ችግሮች እልባት መስጠት የሚችሉ ሀሳቦችና የመፍትሔ አቅጣጫዎች ለማግኘት በር የሚከፍት መሆኑን መግለጻቸውን ከሶማሌ ክልል ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.