Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ ለአፋር ክልል 6 ሚሊየን ብር የሚያወጣ የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 14 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ፣ ከነማ ፋርማሲ እና ምግብ መድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ለአፋር ክልል 6 ሚሊየን ብር የሚያወጣ የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አድርገዋል፡፡
 
የአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዮሐንስ ጫላ÷ የተደረገው ድጋፍ በአሸባሪው እና ዘራፊው ህወሓት ቡድን ጉዳት የደረሰባቸውን ጤና ተቋማት ስራ ለማስጀመር የሚደረገውን ጥረት የሚያግዝ መሆኑ ተናግረዋል፡፡
 
ድጋፉ የህክምና መሳሪያዎችን፣ መድሃኒቶችን እና ሌሎች የንጽህና መጠበቂያ ግብዓቶችን ያካተተ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡
 
የጤና ባለሙያዎች ከህግ ማስከበር ዘመቻው ጀምሮ በሙያቸው ግንባር ድረስ በመዝመት አስፈላጊውን ሚና እየተወጡ መሆኑን የገለጹት ሃላፊው ÷ አሁንም የጤና ተቋማቱን ስራ ለማስጀመር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረጉ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
 
እስካሁን ድርስም ከ400 በላይ ጤና ባለሙያዎች እና ከ70 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት መድሃኒትና ሌሎች የህክምና ቁሳቁሶችን ድጋፍ ማድረግ መቻሉን አንስተዋል፡፡
 
የህልውና ዘመቻው በድል እስኪጠናቀቅ ድረስም የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መግለጻቸውን ከቢሮው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.