Fana: At a Speed of Life!

በአሸባሪዎቹ ለተጎዱ አካባቢዎች ልዩ ትኩረት ይሰጣል – የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሸባሪዎቹ ለተጎዱ አካባቢዎች ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት እንደሚሰራ የግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ሰለሞን ላሌ ተናግረዋል፡፡

አሸባሪዎቹ ህወሓት እና ሸኔ በአማራ ፣ አፋር እና ኦሮሚያ ክልሎች ያደረሱትን ጉዳት ታሳቢ ያደረገ እቅድ ተነድፎ መሰራት እንዳለበት ነው ሰብሳቢው ያስገነዘቡት፡፡

ሰብሳቢው ይህንን ያሉት የግብርና ሚኒስቴርን፣ የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስቴርን እና የውሃና ኢነርጅ ሚኒስቴርን የአስር እና አምስት ዓመታት እቅዶች በተገመገመበት ወቅት ነው፡፡

በዚህ ወቅትም በጦርነቱ ጉዳት የደረሰባቸው አካባቢዎች የኤሌክትሪክ ሃይል ፣ ንጹህ የመጠጥ ውሃ እና የግብርና ግብዓት አቅርቦቶች ስርጭት እንዲኖር ሶስቱም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች የጋራ እቅድ አውጥተው ተቀናጅተው መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል ፡፡

ሰብሳቢው አክለውም፥ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶቹ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሀብት የሚፈስባቸው ተቋማት እንደመሆናቸው መጠን ብልሹ አሰራሮችን በመታገል ፍትሃዊ እና ተደራሽነት ያለው አገልግሎት እንዲሰጡ በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባም ነው ያስረዱት፡፡

የየሚኒስቴር መስሪያ ቤቶቹ የስራ ኃላፊዎች በበኩላቸው ፥ በጦርነቱ ጉዳት የደረሰባቸው አካባቢዎች የመብራት ፣ የንጹህ የመጠጥ ውሃ እና አስፈላጊውን የግብዓት አቅርቦቶች እንዲያገኙ የጋራ እቅድ አውጥተው እንደሚሰሩ መግለጻቸውን ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.