Fana: At a Speed of Life!

ፖላንድ የአውሮፓ ህብረት የስልጣን ገደብ ሊኖረው እንደሚገባ አሳሰበች

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 14 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፖላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ማቴሽ ሞራዊኪ የአውሮፓ ህብረት የስልጣን ገደብ ሊኖረው ይገባል ሲሉ ህብረቱ በፖላንድ ላይ ህጋዊ እርምጃ እወስዳለሁ ማለቱን ኮንነዋል፡፡

የአውሮፓ ህብረት ትናንት በፖላንድ የህግ ጥሰት ተፈጽሟል፤ በቀዳሚነትም የአውሮፓ ህብረት ህግ ተጥሷል ለዚህም ህጋዊ እርምጃ እንወስዳለን ማለቱ ይታወሳል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደሚሉት የአውሮፓ ህብረት ሉአላዊ አገር ውስጥ ገብቶ እርምጃ እወስዳለሁ ማለቱ ተቀባይነት የሌለው ከመሆኑም በላይ የህግ ጥሰት ነው፡፡

የፖላንድ ሕገ-መንግሥታዊ ፍርድ ቤት ከአውሮፓ ህብረት ይልቅ ለፖላንድ ህጎች ቅድሚያ በመስጠት ሁለት ውሳኔ አሳልፏል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩም “እኔ እንደማስበው የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት ሊወስኗቸው የሚችሉባቸው ጉዳዮች ገደብ ሊኖራቸው እንደሚገባ ሊያስተውሉ ይገባል” ብለዋል፡፡

በእርሳቸው አስተያየት አብዛኛዎቹ የአውሮፓ ዜጎች የአውሮፓ ህብረት እንደ የቤተሰብ ህግ ወይም የውርስ ህግ ባሉ አንዳንድ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ እንዲያደርግ አይፈልጉም፡፡

አያይዘውም እየጨመረ የመጣው ቢሮክራሲያዊ አካሄድ ዝንባሌ አንድ ቦታ መቆም እንዳለበት ጠቁመው የአውሮፓ ኮሚሽን በአባል ሀገራቱ እና በብራስልስ መካከል ያለው ልዩነት ግልጽ የሆነለት አይመስልም ማለታቸውን አርቲ ዘግቧል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.