Fana: At a Speed of Life!

ዶ/ር ጥላሁን ጎሹና አጋሮቻቸው 4 ነጥብ 8 ሚሊየን ዶላር የሚያወጡ የህክምና ግብዓቶችን ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ የሚኖሩት ዶክተር ጥላሁን ጎሹ እና አጋሮቻቸው ከነትራንስፖርታቸው 4 ነጥብ 8 ሚሊየን ዶላር የሚያወጡ የህክምና ግብዓቶችን ድጋፍ አድርገዋል፡፡
 
በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍጹም አረጋ፥ኢትዮጵያውያኑ ያደረጉት ድጋፍ በሰሜን ኢትዮጵያ ክፍል በሽብር ቡድኑ ህወሓት የወደሙ የጤና ተቋማትን መልሶ ለመገንባት የሚውሉ መሆናቸውን በትዊተር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል፡፡
 
የተደረገው ድጋፍም የህክምና መሳሪያዎችን፣ የህክምና ቁሳቁሶችን፣ ቪታሚኖች እና አንድ ኮንቴነር ሙሉ መድሃኒቶችን ያካተተ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
 
አምባሳደር ፍጹም የህክምና ግብዓቶቹ በመርከብ ወደ ኢትዮጵያ መላካቸውን በመግለጽ፥ የምህረት ሜዲካል አቅራቢ ባለቤት ዶክተር ጥላሁን ጎሹ እና አጋሮቻቸው ላደርጉት ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.